የሀገር ውስጥ ዜና

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ለኢትዮጵያ የአንበጣ መከላከል ስራ የ800 ሺህ ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ ነው

By Tibebu Kebede

January 31, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) ኢትዮጵያ እያካሄደች ላለው የበረሃ አንበጣ መከላከል ስራ የ800 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

የዓለም እርሻና ምግብ ድርጅት (ፋኦ) በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ በተመለከተ ባዘጋጀው የውይይትና ድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ድርጅቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።