2 ሺህ 281 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የሚገኙ 2 ሺህ 281 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ነው።
ተመላሾቹ በኬንያ የተለያዩ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ከሶስት እስከ አራት አመታት የቆዩ ናቸው።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሚመለሱት ስደተኞች፥ በኬንያ ካኩማና ዳዳብ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች የቆዩና ለመመለስ ፈቃደኛ የሆኑ ናቸው ተብሏል።
ዜጎቹን ከከፋ ችግርና እንግልት ለመታደግ በሚከናወነው ስራ ከካኩማ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ 85 እንዲሁም ከዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ደግሞ 2 ሺህ 196 ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሰነድ ተዘጋጅቶላቸው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ እየተሰራ ነው።
ለዚህም በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቅድመ ዝግጅት ስራውን አጠናቆ የጉዞ ሰነድ ለተመላሾች እየሰጠ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።