የሀገር ውስጥ ዜና

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለተቋሙ ስኬት ጥረት ላደረጉ አካላት የእውቅና መርሃ ግብር እያካሄደ ነው

By Meseret Awoke

August 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የ2021 የሄርት ኮንቬንሽን ተሸላሚው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለተቋሙ ስኬት ያለሰለሰ ጥረት ላደረጉ ሰራተኞች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም እያካሄደ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደዉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ምርምር፣ የቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን አሸናፊ መሆኑን ምክንያት በማድረግ የምስጋና እና የእውቅና አሰጣጥ መርሃግብር እያካሄደ ነው፡፡

በመርሀ ግብሩ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ ለተገኘው ስኬት የእንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት አስተላልፈው÷ ተቋሙ ከ12ቱ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በአፈፃፀም፣ በአመራርና በፈጠራ አሸናፊ እንዲሆን ከፅዳትና ከውበት ሰራተኞች እስከ ከፍተኛ የተቋሙ አመራሮች ሁሉም የበኩሉን ጠጠር በማቀበሉ ነው ብለዋል።

የተኘውን ስኬት ከመዘከር ባሻገር እንዴት ማስቀጠል ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ የተገኙ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱላኪም ሙሉ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት÷ የሐይማኖት አባቶች ፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣መምህራን፣ ተመራማሪዎች እና የተቋሙ ሰራተኞች ተገኝተዋል።

በወርቃአፈራው ያለው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!