ስፓርት

ፋሲል ከነማ ለጠለምትና አዲአርቃይ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

August 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ ለጠለምትና አዲአርቃይ ተፈናቃይ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ፋሲል ከነማ ከአዲአርቃይና ጠለምት አካባቢዎች በህልውና ማስከበር ዘመቻው ምክንያት በደባርቅ ከተማ በጊዜያዊነት ለተጠለሉ ከ16 ሺህ በላይ ወገኖች የልብስና የምግብ ቁሳቁስ ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡

ድጋፉን ያበረከቱት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማህበር ፕሬዚደንት ወጣት ሃይለማርያም ፈረደ ÷ ለወገኖቻችን ለጊዜው ይሆን ዘንድ ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊትም በጋይንት ግንባር ለተሰለፈው የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እንዲሁም ፋኖ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሃኑ ወገኖቻችን በችግር ላይ ሆነው ቆመን መመልከት የለብንም ብለዋል፡፡

ድጋፉ ከክለቡ ተጫዋቾች፣ የስታፍ አባላት እና ደጋፊዎች መሰብሰቡን ከሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይም ይህ የህልውና ዘመቻ እንኪጠናቀቅና ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ ድረስ ለማገዝ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!