የሀገር ውስጥ ዜና

ሶስት ወንድማማቾች በአሸባሪው ህወሓት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

By Meseret Awoke

August 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሶስት ወንድማማቾችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

የሽብር ቡድኑ ወደ ጋይንት ገብቶ በቆየባቸው አስር ቀናት በሀይል ከተደፈሩ ሴቶች÷ ከዘረፈው ንብረት ውጭ ንፁሃንን በመረሸን ዘመን የማይሽረው ጠባሳ በነዋሪዎች ላይ አሳድሯል።

ሟቾቹ በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ የነፍስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች ነበሩ።

በወቅቱ መንገድ ላይ የነበሩትን ሙላት መንገሻ፣ ይበልጣል ባየ እና ገብሬ ተስፋ የተባሉትን የአንድ ቤተሰብ አባላት ቤተሰብ ጠይቀው ሲመለሱ መሳሪያ ሳይታጠቁ ‘‘ተማርካችኋል እጅ ስጡ’’ በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽኗቸዋል።

የሟች ቤተሰቦች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ‘‘የሶስቱን አስከሬን አናስነሳም፣ አታለቅሱም’’ በማለት ለሶስት ቀን ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

ከሟቾቹ መካከል ሙላት መንገሻ በግል ድርጅት ተቀጥሮ የሚሰራ እና ሟቾችን ጨምሮ ሌሎች አናት አባት የሌላቸውን ቤተሰቦች ያስተዳድሩ ነበር።

የሽብር ቡድኑ ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኋላም ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ ንብረታቸውን ሙሉ በሙሉ ዘርፏቸዋል።

የሟች ሙላት መንገሻ ባለቤት ወይዘሮ ቦሴ ገላው በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት የተረፈ ሀብት ስለሌለ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

በዙፋን ካሳሁን እና በምን ይችል አዘዘዉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!