Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከወትሮው በተለየ በአንድነት ቆሟል – ዶ/ር አለሙ ስሜ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ሁሉም ኢትጵያውያን ከወትሮው በተለየ በአንድነት ቆሟል ሺሉ በሚኒስትር ማእረግ የዲሞክራሲ ሰርአት ግንባታ አሰተባባሪ ዶክተር አለሙ ስሜ ገለጹ፡፡

ይህ የተባለው የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአማራ ልዮ ሀይልና ሚሊሻ ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ነው።

በወሎ ግንባር የተገኙት ዶ/ር አለሙ ስሜ አሸባሪው ህወሀት ዳግም አንሰራርቶ የጥፍት ሴራውን እንዳይሸርብ በጸጥታ ሀይሉ ክፉኛ እየተመታ ነው ብለዎል።

አሸባሪው ቡድን ዳግም በማይነሳበት ሁኔታ እየወደመ ነው ያሉት ዶ/ር አለሙ ኢትያጵውያን በጋራ በመሆን ቡድኑን ለመቅበር የሚያደርጉት ጥረት የሚበረታታ ነው ያሉ ሲሆን÷ ድሉ የኢትዮጵያ ነው ብለዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ÷ ዞኑ ከ20 በላይ በሬዎችንና ከ100 በላይ በጎችን በወሎ ግምባር ለሚገኘው የጸጥታ ሀይል ማስረከቡን ገልጸው አሽባሪው እስኪደመስስ ድረስ የማህበረሰቡ ድጋፍ ይቀጥላል ብለዋል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.