Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ በባለሀብቶችና በበጎ ፍቃደኞች 89 የመማሪያ ክፍሎች ተገነቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ በዚህ አመት በባለሀብቶችና በበጎ ፍቃደኞች በ44 ሚሊየን ብር ወጪ 89 የመማሪያ ክፍሎች መገንባታቸው ተገለፀ።

ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠልም በቀጣይ አመት በ102 ሚሊየን ብር 12 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ታቅዶ ዛሬ የዲዛይንና የካርታ ርክክብ ተደርጓል።

ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡት በከተማው ባለሃብቶች፣ በእምነት ተቋማት፣ ውጭ በሚኖሩ ዳያስፖራዎች፣ በማህበራትና ወጣቶች ተሳትፎ መሆኑ ታውቋል።

በጅማ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ቤቶች ማሻሻል የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ጉተማ ግዲ÷ በዚህ አመት የተገነቡ የመማሪያ ክፍሎች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ገልጸው በቀጣይ አመት ለመገንባት የታቀዱት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን በአንድ አመት ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ትጃኒ ናስር በበኩላቸው ÷የተሻለና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመፍጠር ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በመሆኑም የከተማው መስተዳድር የከተማውን ነዋሪዎችና ባለሃብቶች በማስተባበር የሚያደርገውን የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት ግንባታ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሙክታር ጠሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.