የሀገር ውስጥ ዜና

በትምህርት ዘርፍ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ የአመራር ብቃትን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ

By Alemayehu Geremew

August 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ዘርፍ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ የአመራር ብቃትን የማሳደግ ስራዎችን ማጎልበት እንደሚገባ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ `ታርጌት ኢትዮጵያ` ባዘጋጀው አውደ-ጥናት ላይ እንደተናገሩት÷ የትምህርት ስራን ለማሳደግ በየደረጃው ብቃት ያለው አመራር መኖሩ ወሳኝ ነው።

ሳይንሳዊ እውቀትና የጠራ ግንዛቤ ያለው አመራር ፈተናዎችን በመሻገር የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል።

በመሆኑም በየደረጃው የሚገኝ የትምህርት ዘርፍ አመራር ብቃቱን በማሳደግ ራሱንና አካባቢውን ብሎም ሀገሩን ለወለወጥ መስራት እንደሚጠበቅበት ማስገንዘባቸው ተገልጿል።

የ`ታርጌት ኢትዮጵያ` የኢትዮጵያ ተጠሪ፣ ዶክተር አብዱ ዘለቀ በበኩላቸው÷ የትምህርት ዘርፍ አመራሩን ብቃትና አቅም ለማሳደግ ድርጅታቸው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅትም በመፈጸምና ማስፈጸም አቅም ማሳደግ፣ ርእሰ መምህርነትን ሙያዊ የማድረግ ፣ የአመራር ብቃት ማሳደግና ክትትልና ግምገማን መሠረት ባደረጉ አራት መስኮች በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

በአውደጥናቱ በአራቱ ታዳጊ ክልሎች በናሙናነት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተካሄደው የሙከራ ትግበራ ውጤት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት እንደሆነም ነው ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!