Fana: At a Speed of Life!

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዝና ልውውጥ ስርአት መሻሻል አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2014 የትምህርት ዘመን እቅድና የመረጃ አያያዝ ስርአት ላይ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶችና ባለሃብቶች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት አካሄደዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋ ፥ ባለፈው አመታት መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ተደራሽነት፣ ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡

የውይቱም ዓላማ  የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረትን በመፍታት ኢትዮጵያ  ካለችበት ድህነት ማውጣት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር  የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጅዎችን እና ሪፎርሞችን በመስራት ሲደግፍ ቆይቷል ብለዋል፡፡

በተፈለገዉ መንገድ ብቃት ያለው ዜጋ የመረጃ ጥራት ችግር፣ የመረጃ ልውውጥ እና የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥ ችግሮች በግል ከፍተኛ ትምህርት ክፍተቶች መኖራቸውን ገልጸው፥ ይህ 2014 ዓ.ም ተቀራርቦና ተግባብቶ በመስራት ማስተካከል ይገባል ማለታቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.