የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሳዑዲው ልዑል ጋር በስልክ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

August 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳዑዲው ልዑል፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅት በሁለትዮሽና የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የሳዑዲ ጋዜጣ ዘገባ የመላክታል።

የሳዑዲው ልዑል በውይይቱ ወቅት ለኢትዮጵያ ህዝብ እድገትና ብልጽግና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ደግሞ ስኬትን ተመኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!