Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በላይ ጋይንት ያወደመው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተደረገለት ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በላይ ጋይንት ያወደመው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተደረገለት መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቡድኑ በነፋስ መውጫ የሚገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጨምሮ በሌሎች የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽን መስመር ጥገና ክፍል ቡድን መሪ እንድርያስ ሽፈራው ገልጸዋል።

አቶ እንድርያስ ከጥጥራ እስከ ነፋስ መውጫ ተዘርግቶ የነበረው ከ30 ኪሎ ሜትር በላይ የኤሌክትሪክ መስመር በጥፋት ቡድኑ መውደሙንም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ከባድ የዝናብ ወቅት ቢሆንም የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባለሙያዎች መስመሩን ለመጠገን ሌት ከቀን እየሠሩ መሆኑን ቡድን መሪው አስረድተዋል።

የጉዳት መጠኑ ሠፊ በመሆኑ ከፍተኛ ወጪ እንደሚፈልግም ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.