Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የምርት ዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 657 የንግድ ተቋማት ፈቃዳቸው ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የምርት ዋጋ ማናር ላይ የተሰማሩ 657 የንግድ ተቋማት ፈቃዳቸው መሰረዙን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው በወቅታዊ ንግድና ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት÷ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የምርት ዋጋ ማናር ላይ በተሰማሩ 1ሺህ 886 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስደዋል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው የንግድ ተቋማት መካከል 657ቱ የንግድ ፈቃዳቸው መሰረዙን ኢፕድ ዘግቧል።

እንደቢሮ ኃላፊው ገለጻ÷ በከተማዋ በተደረገው የቁጥጥር ስራ 369 መጋዘኖች ላይ ፍተሻ ተደርጓል።

በዚህም 20 መጋዘኖች ላይ ያለአግባብ የተከማቸ ምርት በመገኘቱ መጋዘኖቹ መታሸጋቸውን ሃላፊው ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.