የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ለአትሌት ትዕግስት ገዛህኝ መንግስቱ የእንኳን ደስ አለሽ መልዕክት አስተላለፉ

By Meseret Awoke

August 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፓራሊምፒክ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ ላስገኘችው አትሌት ትዕግስት ገዛህኝ የእንኳን ደስ አለሽ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ‘’ትዕግስት ገዛሀኝ መንግስቱ በሴቶች 1,500 ሜትር በማሸነፍና በፓራሊምፒክ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ለማስገኘት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አትሌት በመሆኗ እንኳን ደስ ያለሽ’’ ብለዋል።

‘’ኢትዮጵያ ኮርታብሻለች’’ ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

በቶኪዮ 2020 ፖራሊምፒክ ውድድር በ1500 ሜትር T-13 አይነስውራን ጭላንጭል ምድብ የፍፃሜ ውድድሯን ያደረገችው አትሌት ትዕግሥት ገዛኸኝ 04:23:24 በሆነ ሰዓት በመግባት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

የ21 ዓመቷ ትዕግስት በድንቅ ብቃት አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት በፖራሊምፒክ ጨዋታ አዲስ ታሪክ ለኢትዮጵያ አስመዝግባለች፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!