Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከፈረንሳይ ፓርክ እስከ ፈረንሳይ አቦ ድረስ ያለው መንገድ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከፈረንሳይ ፓርክ እስከ ፈረንሳይ አቦ ድረስ ያለው መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዛሬው እለት በስፍራው ተገኝተው የመንገዱን ግንባታ ተመልክተዋል።

በዚሁ ወቅትም ኢንጂነር ታከለ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ የተለያዩ የመሰረልማት ጥያቄዎች እና ከመንገዱ ግንባታ ጋር በተያዘዘ የወሰን ማስከበር ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል።

የተነሱ የውሀና የመብራት ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያገኙ እንዲሁም የወሰን ማስከበር ጥያቄዎችም ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ምክትል ከንቲባው ከቀናት በፊት ቃል በገቡት መሰረት የመንገዱ ግንባታ በፍጥነት በመጀመሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ ችግሮችን ለመፍታት እያሳየ ላለው ጥረት አመስግነዋል።

የመንገዱ ግንባታ የረጅም አመታት የአካባቢው ነዋሪዎች ጥያቄ የነበረ እንደሆነም የከንቲባ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

መንገዱ 1 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሲሆን 15 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖር ተደርጎ የሚገነባ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.