ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሂቺሌማ የቀድሞ ሹማምንቶችን አሰናበቱ

By Alemayehu Geremew

August 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ የሀገሪቷን ከፍተኛ የጦር ሹማምንት እና የፖሊስ ኃላፊ በአዳዲስ መተካታቸው ተሰማ፡፡

የፕሬዚዳንቱ እርምጃ የፀጥታ አካላት ለዜጎች የበለጠ ኃላፊነት ተሰምቷቸው ስራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የሃገሪቱን አዲስ የጦር፣ አየር ኃይል እና ብሔራዊ አገልግሎት ሹማምንቶቻቸውን እና ምክትሎቻቸውን እንዲሁም የፖሊስ ሃላፊዎችን ይፋ አድርገዋል፡፡

ሂቺሌማ አዲሶቹ የቢሮ ኃላፊዎች የዜጎችን ሰብአዊ መብት እና ነፃነት በማክበር ሀገራቸውን በትጋት እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ፖሊሶች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት አስፈላጊውን ፍተሻ እና የማጣራት ስራ ማከናወን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ሁሉም የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች ከኃላፊነታቸው ቢነሱም ተተኪዎቻቸው ግን አልተገለፁም።

በከፍተኛ ድምፅ የተመረጡት የአሁኑ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ቀደም ሲል በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ ሲደርስባቸው እንደነበር እና ለበርካታ ጊዜያት በእስር እንደቆዩ ቢቢሲ አስታውሷል፡፡