የሀገር ውስጥ ዜና

የመተከል ዞን ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ስንቅ አዘጋጁ

By Feven Bishaw

August 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመተከል ዞን ሴት የመንግስት ሰራተኞች እና የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ስንቅ አዘጋጁ፡፡

የዞኑ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ እናትነሽ ማሩ ÷በዞኑ ውስጥ ሰላምን ለማስከበር ተሰማርቶ ለሚገኙ የሰራዊት አባላት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ከመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ጋር በመተባበር እየተከናወነ ያለው የስንቅ ዝግጅት ለሰራዊቱ ደጀን በመሆን አጋርነት የሚያሳይ እንደሆነ ሃላፊዋ አብራርተዋል።