ኤጀንሲው ከመንግስትና ከግል ባንኮች ጋር ለመስራት ተስማማ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ ካሉ 15 ባንኮች ጋር ሰነዶችን በቀጥታ ለማረጋገጥ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
ተቋሙ የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማዘመን ላይ እንደሚገኝ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ገልጸዋል።
ተቋሙ ከሁሉም የሀገሪቱ ባንኮች ጋር እያደረገ ያለው የቀጥታ የመረጃ ልውውጥ ስምምነትና ትግበራ የተገልጋዩን ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበት የሚቆጥብ እና የዜጎችን ሃብትና ንብረት ከአጭበርባሪዎች ለመጠበቅ እንደሚያግዝ መግለፃቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!