የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ከምስራቅ ዕዝ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን ሚሊሻዎች አስመረቀ

By Tibebu Kebede

August 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስሪያ አብደላ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ለመበተን አስቦ የከፈተውን ጦርነት በተባበረ ክንድ በመመከት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የዛሬ ተመራቂ የፀጥታ ሃይሎችን ጨምሮ ሁሉም የፀጥታ ሃይሎች በጥምረት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህ በበኩላቸው፥ ሽብርተኞቹ ህወሓት እና ሸኔ የጋረጡትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም ሰው እያደረገው ካለው ርብርብ በተጨማሪ የፀጥታ ሃይሎች በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል።

የሐረሪ ክልል የዛሬ ተመራቂዎችም የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ በተጨማሪ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በመስራት የሽብርተኞችን እንቅስቃሴ ማክሸፍ እንደሚገባ መናገራቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

የሐረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ናስሩ ዩያ፥ ሰልጣኞቹ በስልጠና ያገኙትን ወታደራዊ፣ አካላዊና ፖለቲካዊ አቅምን በመጠቀም በቀጣይ ሊሰጣቸው የሚችለውን ተልዕኮ በብቃት እንደሚወጡ እምነቴ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!