የሀገር ውስጥ ዜና

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

By Feven Bishaw

August 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻ የሚውል ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት ዓፀደወይን ተቋሙ በ2013 ዓ.ም ከመማር ማስተማሩ በተጓዳኝ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ መልካምና አበረታች ስራዎች መስራቱን ገልፀዋል፡፡