የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ወሎ ዞን የወጣቶች የክተት ዘመቻ መድረክ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

August 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ወሎ ዞን የወጣቶች የክተት ዘመቻ መድረክ በመቅደላ አምባ ዮኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የአማራ ክልል የዞን እና የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን÷ የክተት አዋጁን ተቀብለው የተቀላቀሉ ከ1 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ወጣቶችም ተሳታፊ ናቸው።

በውይይት መድረኩ ወጣቶች የሀገራቸውን ህልውና የመጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት ተላልፏል።

በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ ዶክተር አለሙ ስሜ እንዲሁም የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሀመድ ተገኝተዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ፣ በከድር መሀመድና በመሀመድ አሊ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!