የሀገር ውስጥ ዜና

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Demissu

August 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠመራ ዩኒቨርሲቲ በአፋር ክልል ኪልባቲ ዞን በራህሌ ወረዳ ላይ በጁንታው ጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብ እርዳታ አድርገዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱረህማን ከድርን ጨምሮ የዩንቨርስቲው አመራሮች ቦታው ድረስ በመሄድ እርዳታውን እንዳስረከቡ ለማወቅ ችለናል።

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አሁን በአፋር ህዝብ ላይ የተጋረጠባቸው የተለያዩ ችግሮች በተጠና መልኩ እየፈታ  እንደሚገኝ ከዩኒቨርስቲው የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!