ዓለምአቀፋዊ ዜና

ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ሰው በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ

By Tibebu Kebede

February 02, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፊሊፒንስ ከቻይና ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈው የ44 ዓመቱ ቻይናዊ ወደ ፊሊፒንስ ከመጓዛቸው በፊት ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተቀሰቀሰበት ውሃን ከተማ ነዋሪ እንደነበሩ ተገልጿል።