የሀገር ውስጥ ዜና

በከተማ ግብርና አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

By Feven Bishaw

September 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ ግብርና ዘርፉ የሚገኘው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰሰሩት ፅሁፍ÷ “ከተማችን የከተማ ግብርና ልምድ እንዲዳብር፣ ከዘርፉ የሚገኘው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን እያከናወንን ስለሆነ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ ጀምረናል” ብለዋል።