Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ፣ ሐረሪ እና ደቡብ ክልሎች ለሚካሄደው ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ፣ ሐረሪ እና ደቡብ ክልሎች መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚካሄደው ድምጽ አሰጣጥ የመራጮች ምዝገባ መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡
በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዩ ጉልህ ግድፈቶች፣ በመራጮች ምዝገባ ላይ በቀረቡ አቤቱታዎች እና ከጸጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ምክንያት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ምርጫ ያልተደረገባቸው ቦታዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ቀሪ ምርጫ ባልተከናወነባቸው የምርጫ ክልሎችን የፊታችን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድምጽ የሚሰጥ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
ይህን ተከትሎም 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው በሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በደቡብ ክልል አንዳንድ ቦታዎች መስከረም 20 ለሚካሄደው ድምጽ አሰጣጥ የመራጮች ምዝገባ መጀመሩን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

 

የመራጮች ምዝገባም ከነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.