ስፓርት

ቢሾፍቱ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች የአለምዘርፍ የኋላና በወንዶች ታምራት ቶላ አሸፈንፈዋል

By Tibebu Kebede

February 02, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ  ከተማ ዛሬ በተካሄደው13ኛው የኢትዮጵያ የግማሽ ማራቶን ውድድር   በሴቶች አትሌት የአለምዘርፍ የኋላ እንዲሁም በወንዶች ታምራት ቶላ ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።

ውድድርሩ  ፖላንድ ለሚካሄደው የአለም የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን  ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ለክልሎችና፣ለከተማ አስተዳደሮች፣ ለክለቦች እና ለተቋማት የውድድር እድል በመፍጠር ተተኪ አትሌቶችን ማፍራት ያስችላል ነው የተባለው።

በዚህም በሴቶች ምድብ የአለምዘርፍ የኋላ ከአዋሳ ከነማ ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፥ ብርሃኔ ዲባባ ከኦሮሚያ ፖሊስ እንዲሁም አበባ የሻነህ ከአማራ ፖሊስ  ተከታትለው በመግባት  2ኛ እና3ተኛ  ሆነው አጠናቀዋል።

እንዲሁም በወንዶች ምድብ በተደረገ ውድድር  አትሌት ታምራት ቶላ ከኦሮሚያ ፖሊስ ውድድሩን  በአንደኝንት ሲያጠናቅቅ ፥ ልዑል ገ/ስላሴ እና አምደወርቅ ዋለልኝ  በግል ተከታትለው በመግባት  2ኛና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በውድድሩ በሁለቱም ጾታዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የ100 ሺህ ብር ሽልማት እንደተሰጠ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በውድድሩ የተሻለ ውጤት ያስመዘዘገቡ ተወዳዳሪዎችበፖላንድ ዲንያ ከተማ በሚካሄደው 24ኛው የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያን  ወክለው እንደሚሳተፉ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።