የሀገር ውስጥ ዜና

የገቢዎች ቢሮ ደረሰኝ ብቻ በመሸጥ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Feven Bishaw

September 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አገልግሎት ሳይኖራቸው ደረሰኝ ብቻ በመሸጥ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደደረሱ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ከዚህ ቀደም እቃ ወይም አገልግሎት ሳይኖራቸው ደረሰኝ ብቻ በመሸጥ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው በሚል ጥቆማ ቀርቦባቸው እና መረጃ ተሰባስቦባቸው የቆዩ ድርጅቶች ላይ በተከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ሁለት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች፣ በሁለት ደረሰኞች ብቻ 29 ሚሊየን 940 ሺህ 135 ዋጋ ያለው ደረሰኝ ሲሸጡ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በተሰራ ኦፕሬሽን እጅ ከፍንጅ ሊያዙ ችለዋል፡፡