የሀገር ውስጥ ዜና

በቤሩት ያለሰነድ ይኖሩ የነበሩ 35 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

By Tibebu Kebede

September 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤሩት ያለሰነድ ይኖሩ የነበሩ 35 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ተመለሱ።

ዜጎቹ የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ከሊባኖስ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ጋር በመነጋገር ነው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት።

በዛሬው እለት ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ባለፈው አመት ታህሳስ ወር ላይ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የተመዘገቡና የህክምና ማስረጃ ያቀረቡት መሆናቸውን በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!