የሀገር ውስጥ ዜና

ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነትና ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች

By Tibebu Kebede

September 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ከኩባ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናያንሲ ሮድሪጌዝ ጋር በሁለትዮሽና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ኩባ ለኢትዮጵያ በብዙ መስክ ያደረገችውን ድጋፍ አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ከኩባ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ያነሱት አምባሳደሩ፥ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር እንዲሁም የትግራይን ጉዳይ በሚመለከት ገለፃ አድርገውላቸዋል።

የኩባ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናያንሲ ሮድሪጌዝ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ለተደረገላቸው ገለፃ ምስጋና አቅርበው፥ ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ችግሮች በፅናት እንደምታልፋቸው እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አናያንሲ ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር በተለያዩ መስኮች አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!