የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሀርጌሳ ገቡ

By Tibebu Kebede

September 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሶማሊ ላንድ ሀርጌሳ ገቡ።

ለአምባሳደሩ የሶማሊ ላንድ የውስጥ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሊባን ዩሱፍ እና በሀርጌሳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አምባሳደር ሰኢድ መሀመድ እና ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አምባሳደሩ በተለያዩ ጉዳዮች ከሶማሊ ላንድ አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የሶማሌ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!