የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገች

By ዮሐንስ ደርበው

September 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ዱቄትና ዘይት ለተፈናቃዮች ድጋፍ አድርጋለች፡፡

አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች ነው ቤተክርስቲያኗ ድጋፍ ያደረገችው፡፡