የሀገር ውስጥ ዜና

የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ለህልውና ዘመቻው በግንባር በመገኘት ድጋፍ አደረጉ

By Alemayehu Geremew

September 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ የሚኖሩ የተለያየ ማሕረሰብ ተወካዮች ግንባር ድረስ በመሄድ የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ለሠራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት ለማሳየት በተወካዮቻቸው አማካኝነት በግንባር በመገኘት ባስረከቡበት ወቅት÷ አረመኔው የሽብር ቡድን እስከሚደመሰስ ድረስ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሰራዊት አመራር አባላት በበኩላቸው÷ የደሴ ከተማ ህዝብ ደጀንነቱን ለማስመስከር ያደረገውን ድጋፍ አድንቀው÷ ድጋፉም ከድጋፍነት የተሻገረ ትርጉም ያለው እንደሆነና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ይኸው ድጋፍም አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በመደምሰስ ሂደት ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው ነው የተናገሩት፡፡

ድጋፉን ለማድረስ ግንባር ድረስ የተገኙ የከተማዋ ነዋሪ ተወካዮችም÷ ከምንም በላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገር ህልውና እየከፈለ ያለውን ዋጋ መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡

 

 

በሐብታሙ ተክለሥላሴ