የሀገር ውስጥ ዜና

ህልውናችንን አደጋ ላይ ለመጣል የተነሱ ቡድኖችን ለመመከት ያለልዩነት መስራት ይገባል-ምሁራን

By Meseret Demissu

September 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የውስጥ አንድነት አደጋ ላይ ለመጣል የተነሱ ቡድኖችን ለመመከት ያለልዩነት መስራት ይገባል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።

የፍልስፍና መምህሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ፥ የለውጡ መንግስት በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ የታላቁ የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን ማሳካቱ፣ ለምዕራባውያን የማይጠመዘዝ አቅም መገንባት መቻሉ፣ ሀገር አቀፍ ምርጫን በስኬት ማካሄድ መቻሉ እንዲሁም የዲሞክራሲ ምህዳርን ለማስፋት መቻሉን በአድናቆት ጠቅሰዋል።