የሀገር ውስጥ ዜና

የዲጂታል ግብርና ኤክስቴንሽን ለማቋቋም ውይይት እየተካሄደ ነው

By Meseret Demissu

September 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲጂታል ግብርና ኤክስቴንሽን እና የምክር አገልግሎት ባለድርሻ አካላት ፎረም ለማቋቋም ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የግብርና ኤክስቴንሽኑን አገልግሎት ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የግብርና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የኤክስቴንሽና የምክር አገልግሎቱን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ እየሰራ ነው ተብሏል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ እየተደረገ ያለውን ተግባር ለማጠናከር ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በአዳማ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።

በነገው ዕለትም የተለያዩ አጋር አካላትን ያማከለ የዲጂታል ግብርና ኤክስቴንሽን እና የምክር አገልግሎት ባለድርሻ አካላት ፎረም ይቋቋማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከግብርና ሚኒስቴር ያገነነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!