የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአፋር ለተፈናቀሉ ዜጎች  ድጋፍ አደረገ

By Meseret Demissu

September 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አበረከተ።

ዩኒቨርሲቲው  ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ እንዲሁም  የአልባሳት ድጋፍ ነው ዛሬ ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያስረከበው፡፡

ከተደረገው ድጋፍ መካከል ባለ 20 ሊትር 100 ጀሪካን ዘይት፣ ባለ 25 ኪሎ 70 ከረጢት ሩዝና መኮሮኒ እንዲሁም ፓስታ ይገኝበታል፡፡

በተጨማሪም 200 ብድድ ልብስና 200 አንሶላ፣150 ፍራሽና ባለ 5 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና ድጋፉ ውስጥ ተካቷል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዚዳንት ልዩ ረዳት ሙክታር ዳውድ፥    ወራሪው እስከሚጠፋ ሁሉም መተባበር አለበት ብለዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱራህማን ከድር በበኩላቸው እንደተናገሩት፥ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሌሎች ዪኒቨርሲቲዎችም በአፋር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!