ስፓርት

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ እንግሊዝ በሰፊ ጎል ስታሸንፍ ስፔን ሽንፈት አስተናግዳለች

By ዮሐንስ ደርበው

September 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተካሄደዋል።

በአፍሪካ ምድብ ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች አልጄሪያ ጂቡቲን 8 ለ 0፣ ሞሮኮ ሱዳንን 2 ለ 0፣ ኒጀር በቡርኪና ፋሶ 2 ለ 0፣ ማዳጋስካር በቤኒን 1 ለ 0፣ ናሚቢያ ከኮንጎ እንዲሁም ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከታንዛኒያ አንድ አቻ፤ ኬንያ ከኡጋንዳ ያለምን ጎል ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በአውሮፓ ምድብ በተካሄዱ ጨዋታዎች ደግሞ ፖላንድ እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፈዋል፡፡

ፖላንድ አልባኒያን 4 ለ1፣ እንግሊዝ ሃንጋሪን 4ለ0፣ ቤልጂየም ኢስቶኒያን 5 ለ 2፣ ጀርመን ሌችተንስታይንን 2 ለ 0፣ ስዊድን ስፔንን 2 ለ 1፣ ቼክ ሪፐብሊክ ቤላሩስን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

የአውሮፓ ሻምፒዮኗ ጣሊያን ደግሞ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታዋን ከቡልጋሪያ አንድ አቻ በመለያየት ጀምራለች።

ኮሶቮ ከሜዳዋ ውጭ ጆርጂያን 1 ለ 0፣ አይስላንድ በሮማኒያ 2 ለ 0፣ መቄዶንያ ከአርሜኒያ ያለምን ጎል አቻ፣ ሰሜን አየርላንድ ሉቴኒያን 4 ለ 1 እንዲሁም አንዶራ ሳን ማሪኖን 2 ለ 0 በማሸነፍ ማጣሪያውን በድል ጀምረዋል።