የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሃይማኖት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑ ተገለጸ

By Tibebu Kebede

September 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በባሕር ዳር እየመከረ ነው።

በምክክር መድረኩ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

የምክክር መድረኩ ዓላማ ወራሪውና አሸባሪው ቡድን በሃይማኖት ተቋማት ላይ እያደረሰ ባለው ጥቃት ዙሪያ በመነጋገር የጋራ አቋም ለመያዝ ያለመ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ የገጠማት ወቅታዊ ፈተና ከቀደሙ ፈተናዎቿ የተለየ ባይሆንም ከውስጥ ባንዳዎች የተነሳ በመሆኑ ሳንካዎች የበዙበት እንደሆነ በምክክር መድረኩ ተነስቷል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል በከፈተው ወረራ የእምነት ተቋማት ተጎድተዋል እንዲሁም በቅርሶች ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

አሸባሪውንና ወራሪውን ቡድን በተፋጠነ መንገድ በማክሰም የክልሉ ብሎም የሀገሪቱ ስጋት እንዳይሆን ለማድረግ የሃይማኖት አባቶች እና የተቋማቱ ሚና የጎላ ነው መባሉን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!