የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

September 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን በደቡብ ክልል ሰባት ዞኖች ለሚገኙ ከ3 ሺህ በላይ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የሪጅኑ ኃላፊ አቶ ሹሜ አብሽሮ ተቋሙ በማህበረስብ አገልግሎት በርካታ ተግባራትን እንያከናወነ መሆኑን ገልፀው ÷ የዛሬው የድጋፍ መረሃ ግብር የዚሁ አካል ነው ብለዋል፡፡