የሀገር ውስጥ ዜና

እኛ ወጣቶች እያለን ሀገር በገንጣይ ወንበዴ አትበተንም – የደቡብ ወሎ ወጣቶች

By Meseret Awoke

September 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)እኛ ወጣቶች እያለን ሀገር በገንጣይ ወንበዴ አትበተንም ሲሉ የደቡብ ወሎ ወጣቶች ገለጹ፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነው ከራሳቸው ጥቅም መነሻ የጁንታውን ቡድን እንደ ፈረስ ተጠቅመው በሀገራችንና ህዝባችን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ለሚታትሩ ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ንቅናቄ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሀመድ÷ ጨፍጫፊውን ሀይል በመጣበት መንገድ በህዝባዊ ማዕበል ግብዓተ መሬቱ ይፈፀም ዘንድ የክተት ጥሪውን ለተቀበለው ወጣት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማእረግ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ በበኩላቸው÷ በተለያዩ ግንባሮች አሸባሪው ህወሓት ድባቅ እየተመታ ነው ብለዋል፡፡

ጁንታውን በአካል ብቻ ሳይሆን ከፋፋይ ሀሳቡን ሁሉ ላይመለስ የመቅበር ሀላፊነት አለብን ብለዋል፡፡

ተደራጅቶና ታጥቆ መዘጋጀትም የክልሉን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቀላቀል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በአንድነት ናሁሰናይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!