የሀገራችን ጸጋዎች በጥናትና ምርምር ከታገዙ ከኢትዮጵያ አልፈዉ አፍሪካን መቀየር ይችላሉ- ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ ) “የሀገራችን ጸጋዎች በጥናትና ምርምር ከታገዙ ከኢትዮጵያ አልፈዉ አፍሪካን መቀየር ይችላሉ” ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተናገሩ።
በሁሉም ሴክተሮች የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች የስነ ምግባር መርሆዎችን የተከተሉ መሆን እንዳለባቸውም ተገልጿል።
የምርምር ስነ-ምግባር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መድረክ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ “በአገራችን በርካታ ጸጋዎች አሉ፤ እነዚህም በጥናትና ምርምር ከታገዙ ከኢትዮጵያ አልፈዉ፣ አፍሪካን መቀየር የሚችሉ ናቸው” ብለዋል፡፡
ጥናትና ምርምር የስነ ምግባር መርሆዎችን ተከትለው እንዲሰሩ በማድረግ አገርን ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
“የምርምር ተቋማት ጥናትና ምርምር ስንፈቅድ በምን መርህ ላይ ነዉ መሰረት አድርገን የምንሰራዉ የሚለዉን ትኩረት ማድረግና ለሃገር በቀል እዉቀት ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡
አገራዊ መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሆነ የጠቆሙት ፕሮፌሰር አፈወርቅ፤ መመሪያው በጥናትና ምርምር ስራ ከግንዛቤ ዉስጥ የሚገቡ ጉዳዮችን አካትቶ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።
ሳይንስና ኢትዮጵያ አብረዉ የኖሩ ቢሆኑም በምርምርና ቴክኖሎጂ ደግፎ ከመጠቀም አንጻር ሰፊ ክፍተት መኖሩን ገልጸዋል።
“ምርምር ለልማት፣ ለሃብት እና ለሃገር ግንባታ መስራት ያስፈልጋል” ብለዋል።
የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ÷“ስልጠናው የሰልጣኞችን አቅም በመገንባት በተለይም የምርምር ስነ ምግባር የተያያዙ ችግሮች አሉ በመፍታት በኩል በርካታ ጠቀሜታ ይኖረዋል” ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!