የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በአንጋፋው ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Meseret Awoke

September 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአንጋፋው ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸውም÷ ለረጅም ዓመታት ትውልድን በሚያንፁ እና ኢትዮጵያን ከፍ በሚያደርጉ የሙዚቃ ስራዎቹ የምናከብረው አንጋፋው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ሃዘን እገልጻለሁ ብለዋል፡፡

‘’በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ያበረከተልን ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ ፍሬዎቹ በቀጣይ ትውልድን እያነፁ እንዲሁም የሃገርን ከፍታ እያሳዩ የሚዘልቁ ይሆናል’’ ሲሉም ነው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡

በዚህም ለቤተሰቦቹ፣ ለአድናቂዎቹ እና ለኪነ ጥበብ ቤተሰብ በሙሉ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!