የሀገር ውስጥ ዜና

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሡ

By Alemayehu Geremew

September 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ተቋሙ የህልውና ዘመቻው እንዲሳካ በተለያየ መልኩ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

አሸባሪው የህወሀት ቡድን ከማይካድራ ጀምሮ በደቡብ ጎንደርና መተከል የፈፀማቸውን ግፎች በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ጥናትና ምርምሮችን እያደረገ ስለመሆኑም ገልፀዋል።

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና አመራሮች በመጀመሪያው ዙር የደሞዛቸውን ከ10 እስከ 30 በመቶ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በሁለተኛው ዙር ደግሞ የ1 ወር ደሞዛቸውን ከ54 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ እና በመለገስ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-