ፈረንሳይ ወደ ሳህል ቀጠና ተጨማሪ ወታደሮችን ልትልክ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ወደ ሳህል ቀጠና ሃገራት ተጨማሪ 600 ወታደሮችን እንደምትልክ አስታወቀች።
ፓሪስ ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂ ቡድኖች በአካባቢው የሚፈጽሙትን ጥቃት ለመከላከል ነው ተጨማሪ ወታደሮችን የምትልከው።
አሁን ላይ ፈረንሳይ በቀጠናው 4 ሺህ 500 ወታደሮች ያሰማራች ሲሆን፥ የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ለማስከበር ቁርጠኛ አቋም እንዳላትም ገልጻለች።
ወታደሮቹም በያዝነው ወር መጨረሻ ወደ ስፍራው ያቀናሉ ተብሏል።
ምንጭ፡-አልጀዚራ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision