የሀገር ውስጥ ዜና

የደሴ ከተማ ወጣቶች አሸባሪውን ህወሓት ለመፋለም ዘመቱ

By Meseret Awoke

September 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍና ግንባር ገብቶ ለመፋለም የደሴ ከተማ ወጣቶች የህልውና ዘመቻውን ተቀላቀሉ።

ወጣቶቹ የህልውና ዘመቻውን በመቀላቀል ታሪክን እንደሚሰሩ ጠቅሰዋል።

የከተማው ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል÷ ወጣቱ ከተማው ድረስ ጠላት እስኪመጣ ሳይጠብቅ በየግንባሩ በመሰለፍ እያሳየ ያለው ተነሳሽነት ታሪካዊ ነው ብለዋል።

በዛሬው ንቅናቄ የተለያዩ ባለሀብቶች ስንቅ ይዘው በመገኘት ሰራዊቱን አበረታተዋል።

በስንታየሁ መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!