የሀገር ውስጥ ዜና

ህወሓት በአፋር ባደረሰው ጉዳት ለተፈናቀሉ ወገኖች ጂማ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ አደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

September 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር አካባቢዎች በከፈተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ጂማ ዩኒቨርሲቲ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የአፋር ክልልን ከትግራይ ክልል በሚያዋስናቸው የአፋር አካባቢዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በተለያዩ አካባቢዎች ለተጠለሉ ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲደረግ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ጂማ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ማድጉን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡