Fana: At a Speed of Life!

በቡርኪና ፋሶ በታጣቂ በተፈጸመ ጥቃት የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ምዕራብ ቡርኪና ፋሶ ትናንት ምሽት በአንድ ታጣቂ በተፈፀመ ጥቃት የ20 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

ጥቃቱ ከመዲናዋ ኡጋድጉ በስተሰሜን በምትገኘው ባኒ ከተማ ውስጥ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው የተፈጸመ ነው ተብሏል።

የአሁኑ ጥቃት ከሳምንት በፊት በሲልጋጂ ከተማ የ39 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን ጥቃት ተከትሎ የተፈፀመ መሆኑም ተነግሯል።

በአፍሪካ ሳህል ቀጠና ከቅርብ ወራት ወዲህ አክራሪ ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃት እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል።

ጥቃቱ ፈረንሳይ በሳህል ቀጠና ተጨማሪ 600 ወታደሮችን እንደምትልክ ካስታወቀች በኋላ የተፈጸመ ነው።

የአሁኑ የፈረንሳይ ውሳኔ በቀጠናው የሚገኘውን የፈረንሳይ ጦር አባላት ቁጥር ከ5 ሺህ በላይ ያደርሰዋል።

ከፈረንጆቹ 2012 ወዲህ በሳህል ቀጠና በተፈጠረ ግጭት ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.