የሀገር ውስጥ ዜና

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመርቀዋል

By Meseret Awoke

September 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ማስመረቃቸውን ከዩኒቨርሲቲዎቻቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸዉን 3ሺህ 237 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

የሠመራ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎችና መርሃግብሮች ያስተማራቸውን 246 ተመራቂዎችን ያስመረቀ ሲሆን÷ ከተመራቂዎች መካከልም 69ኙ ሴት ተማሪዎች ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በቴፒ ግቢ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 38 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!