የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ 11ቢሊየን ብር ተገኘ

By Meseret Awoke

September 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት በኢንቨስትመንት ዘርፍ በተሰራዉ ስራ 11ቢሊየን ብር መገኘቱን የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በዘርፉ 13 ቢሊየን በር አሳካለሁ በሚል አቅዶ ነበር።

የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አስራት አሰፋ በኢንቨስትመንት ካለው እምቅ ሀብት አንፃር ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ አልተስፋፋም ብለዋል።

እንደ ሀገር የተፈጠሩ የፀጥታ ችገሮች እና አለመረጋጋት ላይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መጨመሩ ዘርፉ እንዲጎዳ አድርጓል ብለዋል።

ይሁንና በበጀት ዓመቱ በክልሉ በሚሰሩ ከ470 በላይ ኢንቨስተሮች ኢንቨስት በማድረጋቸው ለ140 ሺህ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረ ገልጸዋል።

የግል ባለሀብቱ ንብረት የሀገር ሀብት መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ÷ ህብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ለልማቱ አጋዥ እንዲሆን ማድረግ ከሁሉም አመራር እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

የ2014 በጀት ዓመት የኢንቨስትመንት ውጤታማነት ልዩ ትኩረት እንደሚሆን እምነታቸው እንደሆነ ኮሚሽነር አስራት ተናግረዋል።

በነጻነት ሰለሞን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!