የሀገር ውስጥ ዜና

ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍና አጋርነትን ለመግለፅ የሩጫና የእግር ጉዞ ተደረገ

By Feven Bishaw

September 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)እኔም ለሃገሬ ወታደር ነኝ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም፣ መቼም፣ በምንም በሚል መሪ ቃል ዛሬ መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የ5ኪሜ የጎዳና ላይ ሩጫና የእግር ጉዞ ተደርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት ዛሬ ከንጋቱ 12 ከ 30 ጀምሮ በተደረገው የጎዳና ላይ ሩጫና የእግር ጉዞ መርሃ ግብር የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች፣ ተጠሪ ተቋማትና የስፖርት ማህበራት መሳተፋቸውን ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡