የሀገር ውስጥ ዜና

ነገ የኢትዮጵያዊነት ቀን በመላ ሀገሪቱ ይከበራል

By Feven Bishaw

September 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ነገ የኢትዮጵያዊነት ቀን በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ እንደሚውል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ አዘጋጅነት በመላው ሀገሪቱ ” ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ! እዘምራለሁ!” በሚል ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ በማሸብረቅ ፣ ሰንደቅ ዓለማውን በማውለብለብና ከፍ በማድረግ ከጠዋቱ 2 ከ 30 ላይ ለሁለት ደቂቃ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የሚደረግበት ዕለት መሆኑ ተገልጿል፡፡