በወሎ ግንባር የሚገኙ የጸጥታ አካላት ጁንታውን እየቀበርነው ነው ሲሉ ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ጁንታውን እየቀበርነው ነው ሲሉ ተናገሩ።
የጸጥታ ሀይሎቹ ለፍና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጋዜጠኛች ቡድን እንደተናገሩት፥ ጁንታው በደረሰበት ድብደባ እየፈረጠጠ ቢሆንም ባለበት እንዲቀበር እየተደረገ ነው ብለዋል።
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጋዜጠኞች ቡድን በደቡብ ወሎ እና በሰሜን ወሎ ዞን ባደረገው ቅኝት ጁንታው ሰርጎ ገብቶባቸው የነበሩ ቦታዎች እየተለቀቁ መሆኑን ተመልክቷል።
በውርጌሳ አካባቢ ጥቃቱን ሸሸተው የሄዱ የነበሩ የህብረተሠብ ክፍሎች እየተመለሡ መሆኑንም ተመልክቷል።
በቦታው ያገኘናቸው የመከላከያ ሚንስቴር ዴኤታ አቶ ፍሰሀ ወልደ ሰንበት፥ ጁንታው በአጭር ጊዜ ተደምምስሶ ድል ይሆናል ያሉ ሲሆን ሁሉም አካባቢውን በመጠበቅ ጁንታውን በያለበት ሊቀብር ይገባል ብለዋል።
በጋዜጠኞች ቡድን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share